ሶዶ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት

Sodo Woreda Youth and Sports Office

sodoweredayouthsportoffice@gmail.com

ራዕይ፡- በ2022 የወረዳው ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ስፖርትን በሀሉ ያደረገ ጠየናማ ማህበረሰብ መልካም ስብዕና ያለው ወጣት ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆኑ ስፖርተኞች ተፈጥረው ማየት ፡፡

ተልዕኮ፡- የወረዳን ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳፍፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና ህዝባዊ መሰረት ያለውን ስፖርት በማስፋፋት የዜጎችን አካላዊና ኢኮኖሚያዊ ብቃት በመገንባት ያገርን ብልጽግና ማረጋገጥ ፡፡

  • አሳታፊና ፍታሀዊነት፤
  • ግልጸኝነትና ተጠያቂነት፤
  • ፈጠራን ማበረታታት
  • ቅልጥፍናና ውጤታማነት፤
  • የአግልግሎት ጥራት፤
  • ለለውጥ ዝግጁነት፤
  • በቡድን መስራት፤
  • ህዝባዊነት፤
  • በአካል እንቅስቃሴው የጎለበተ ብቁ ዜጋ መሆን እንዲችል በተከፈቱ የወጣት ማዕከላት በመገለገል ስፖርትን የባህሉ አንድ አካል እንዲያደርግ መደገፍ፤
  • ራሱን ከልዩ ልዩ አደንዛዥ ዕጽ/ደባል ሱስ ጠበቆና ተከላክሎ አስተሳሰቡ ያደገ ቡቁና አምራች ዜጋ እንዲሆን ለለውጥ መስራት ፤
  • በኢኮኖሚው ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ በማድረግና የስራ ባህሉን በማሳደግ ዘለቄታ ያለው ተጠቃሚነት እንዲኖረው ማድረግ

ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ስልጣንና ተግባር

  • የወጣቶች መብትና ጥቅም በማስከበር ዙሪያ ግንዛቤና ንቅናቄ መፍጠር
  • ወጣቶችን ሁኔታ የሚያመላክቱ ዝርዝር መረጃዎችን ያሰባስባል ፤ያደራጃል ፤ ለሚመለከተው ያሳውቃል
  • ወጣቶች በወረዳው የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድሎች የተመቻቸላቸው መሆኑን ያረጋግጣል
  • ወጣቶች በልማት መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ስራዓት ግንባታ ላይ ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ
  • በወረዳው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራትን ያስተባብራል፤
  • ወጣቶች በስነ ምግባር የታነጹና አውንታዊ አመለካከት እንዲያጎለብቱ የስብዕና ግንባታ ስራዎች ይሰራል ፤
  • ወጣቶች ማዕከላትን በማስፋፋት ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙ ችሎታቸውና ዝንባሌያቸውን እንዲያጡ ድጋፍ ያደርጋል ፤
  • የስፖርት ውድድሮች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፤ ያስተባብራል ፤
  • የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል/ያስተባብራል ፤ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል
  • የስፖርት ት/ት ስልጠና እንዲስፋፉ ያደርጋል ፤
  • በግል ለሚቋቋሙ የስፖርት ስልጠና ምዕከላት ፍቃድ ይሰጣል ፤ ይመዘግባል ፤ ይሰርዛል ፤
  • 05 ማጠቃለያ ፡- የሶዶ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከዚህ በላይ የተገለጸውን እንደ መነሻና  ጥቅል ሀሳብ በማቅረብ ጽ/ቤቱ በአመታዊ ዕቅዶች በመያዝ ተግባራቸውን በዝርዝርና ስፋት ባለው ሁኔታ በቀጣይ የሚያቀርብ ሲሆን ለመጀመሪያ ደረጃ ስለጽ/ቤቱ ከራዕይና ተልእኮ ጋር በተያያዘ አሁን ያለበትን አቋም በተመለከተ በአጭሩ ባለው ሁኔታ ተገለጸውን ይመስላል፡፡

Contact

Email-sodoweredayouthsportoffice@gmail.com

Telegram-t.me/sodoweredayouthsportoffice