Sodo woreda Milisha Office

የሶዶ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት

Sodo District Militha Office

sodoweredamilishaoffice@gmail.com
  • ዓላማ፡-

የወረዳው ህብረተሰብ ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ሁኔታ በማረጋገጥ የህግ የበላይነትና የዜጐችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በማስከበር፣ መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥና ለልማት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ነው፡፡

  • ራዕይ

የዜጐች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ የህግ የበላይነትና የመልካም አስተዳደር፣ የህዝቡ ሰላም ፀጥታና ደህንነት የተረጋገጠበት ወረዳ ተፈጥሮ እና ለዚሁም ጉልህ ድርሻ የሚያበረክት ጽ/ቤት ሆኖ ማየት፡-

  • ተልዕኮ

አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን ዘመናዊ በማድረግ ጠንካራ የፀጥታ መረጃ ስርዓት በመፍጠር፣ በህብረተሰቡ ንቁ ተሣትፎ የሚታገዝና ብቃት ያለው የፀጥታ ኃይል በማፍራት ግጭቶችን በሃይማኖት ወይም በእምነት ሽፋን የሚፈፀም የአክራሪነትና የጽንፈኝነት አመለካከትን በብቃት በመለየትና በመከላከል የዞወረዳን ፀጥታ፣ ሰላምና ደህንነት መጠበቅና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በማስከበር የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፡፡

እሴቶች የሴክተሩ ሰራተኞች የስራ አመራሩ የሚመሩባቸውና ወደ ፊትም በጋራ ሊከተሏቸው የሚገቡ የግልና የተቋም የአሰራር ፍልስፍናዎች ሲሆኑ ስራ ሂደቱ፡-

    • ለህገ-መንግስቱ ታማኝ መሆን፣
    • የህብረተሰቡን ተሣትፎ ማረጋገጥ፣
    • ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፣
    • የህዝብ አገልጋይነት፣
    • ብዝሃንነትን መቀበልና ማክበር፣
    • ፍትሃዊነትና ሰብአዊነትን መላበስ፣
    • ራስን ማብቃት አዳዲስ አሰራሮችን ማወቅና መጠቀም፣
    • ሙያዊ ስነ-መግባር መላበስ፣
    • ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ትኩረት መስጠት እና ኃላፊነትን መወጣት የሚሉ እሴቶች ናቸው፡፡

የጽ/ቤቱ ሃላፊ አስተያየት /መልእክት/

ጽ/ቤቱ በ2008ዓ/ም የሚሊሻ አደረጃጀትና አስተዳደርን ለመወሰን ባወጣው ደንብ ቁጥር 143/2008 መቋቋሙን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በተልእኮ ረገድ የሚሊሻ ሃይልን የሚመለምል፤የሚያሰለጥን፤ የሚያደራጅና የሚያሰማራ ተቋም ነው፡፡ ከዚህም አንጻር ጽ/ቤቱ ሰላምን ከማስጠበቅ በተጨማሪ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እየመለመለ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ያለ ተቋም ነው፡፡ የህብረተሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥና የልማት ራዕይ እውን ለማድረግ ጠንካራ የተቀናጀ የተደራጀና ዘመናዊ የፀጥታ ሀይል ለመፍጠር የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት በየደረጃው የለው የህብረተሰብ ክፍል ተሳትፎ ማሳደግና አስተዋጽኦ ማጎልበት ተገቢ ነው፡፡

Contact

Email-sodoweredamilishaoffice@gmail.com

Telegram:-t.me/sodoweredamilishaoffice