ሶዶ ወረዳ ደን ጽ/ቤት

Sodo Woreda Forest Office

አቶ ጎሳዬ ወጂ የሶዶ ወረዳ የአካባቢ ጥበቃና ደን ጽ/ቤት ኃላፊ

ራዕይ / VISION /

  • በ2017 ዓ/ም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በወረዳው ተገንብቶ ለኑሮና ለስራ ምቹ አካባቢ ተፈጥሮ ማየት ፡፡

ተልእኮ / MISSION /

  • የአካባቢ ብዝሀ-ህይወትና የደን ሀብት አያያዝ ልማትና አጠቃቀም ለዘላቂ ልማትና ለድህነት ቅነሳ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ስርአትን የማዘጋጀትና ተፈጻሚነቱን የማረጋገጥ፤ምርምርና የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ሽግግርን የማስተባበርና የማካሄድ ፤ትምህርትና ግንዛቤን የማስፋፋት፤ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ትግበራን የማስተግበር ፤የተግባሪዎችን አቅም የመገንባት ፤የደን ኢንቨስትመንትንና ግብይትን የማስፋፋት ፤ሀገሪቷ የተፈራረመችባቸውን ዓለም አቀፍ የአካባቢ፤የደንና የብዝሀ-ህይወት ስምምነቶችን በመተግበር እና ወቅታዊ የአካባቢና የደን ሁኔታ ለውጥ ዘገባን የማዘጋጀት  ተግባራትን ማከናወን ፡፡
  • ለተገልጋዮች ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት፣
  • በእቅድ መመራት፣
  • የተፈጥሮ ሀብትንናአካባቢያችንን መንከባከብ፣
  • የለውጥ ኃይሎችን ማበረታታት ፣
  • ህብረተሰቡን በልማት ማሳተፍ ፣
  • ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም 
  • ሙያዊ ስነ-ምግባር ማስፋፋት፣
  • ፍትሃዊነት፣ሰብአዊነትና ተጠያቂነትን ማስፈን፣
  • ለሀገር በቀል ዕውቀት እውቅና መስጠት ፣
  • የሴቶችና የወጣቶች የልማት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ

 መረጃን ለልማት ማዋል

ዓላማ / OBJCTIVE /

  • በወረዳዉ ደረጃ እየመጣ ያለው ፈጣን እና ፍትሐዊ ልማት ዘላቂና አካባቢያዊ ደህንነትን ያረጋገጠ እንዲሆን ማስቻል፡፡
  • በ2017 ሐገሪቱ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ በምታደርገው እንቅስቃሴ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስልት ትግበራ
  • በወረዳ ደረጃ የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ ማበርከት

Contact

Email-sodoweredaden@gmail.com

Telegtam-t.me/sodoweredaden