የሶዶ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ፅ/ቤት

Sodo woreda Cultural Tourism Office

አቶ ጌታቸዉ ተካ የሶዶ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ፅ/ቤት ኃላፊ

ዓላማ፡

በወረዳው የሚገኙ ተፈጥሮአዊ ባህላዊ ታሪካዊ መስህቦችና ቅርሶች ለምተው ዘላቂ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገት በማረጋገጥ ለወረደው ነዋሪ ህብረተሰብ የስራ ዕድልና የገቢ ምንጭ በመፍጠር ድህነትን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ሀገራዊ ድርሻ ማበርከት እንዲሁም በወረዳው ቀልጣፋ ውጤታማና ተደራሽ የሆነ የመንግስት የኢንፎርሜሽን ስርዓት በመገንባት መንግስትንና ህዝብን ተጠቃሚ በማድረግ አንድ ፖለቲዊና ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ጉልህ አስተዋፅኦ ማድረግ፤

ተልዕኮ፡

የወረዳው ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የባህል የታሪክ የቋንቋ የቅርስ የተፈጥሮና ሌሎች ባህላዊ ዕሴቶች እንዲጠኑ፤ እንዲጠበቁ፣ በዘላቂነት እንዲለሙና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትትን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ በማሳደግ የቱሪስት መስቦችን በሀገር ውስጥና በውጭ የቱሪዝም ገበያ ለማስተዋወቅ የተቋሙን ልማታዊ ተሳትፎ ማሳደግና የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እና በመንግስት ኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ስርዓት ውስጥ መሪ በመሆን በመንግስትና በህዝብ መካከል ቀልጣፋና ውጤታማ የኢንፎርሜሽን ፍሰት እንዲኖር ማድረግ

ራዕይ ፡-

የባህል ፣ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ቅርስ ተፈጥሮና ሌሎች ባህላዊ እሴቶች ተጠንተው ልምተውና ታውቀው ወረዳው ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ሆኖ ማየት እንዲሁም በኢንፎርሜሽን የበለፀገ በአገር ግንባታ ወሳኝ ተሳትፎ የሚያደርግ ህዝብና የግልፀኝነትና ተጠያቂነት አሰራር የዳበረ መንግስት ተገንብቶ ማየት፤

  • የብሔረሰቦች እኩልነት እናከብራለን
  • ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን እናስከብራለን፤
  • ፍትሀዊነት ተጠያቂነትና አሳታፊነት እናረጋግጣለን፡፡
  • ሙስና እንፀየፋለን፣
  • ተፈጥሯዊ ሀብትንና አካባቢያችንን እንከባከባለን፤
  • ለሀገር በቀል እውቀት ዋጋ እንሰጣለን፤
  • ለሀገር በቀል እውቀት ዋጋ እንሰጣለን፤

ለውጤታማነትና መደጋገፍ እንተጋለን

የተቋሙ ኃላፊ መልዕክት

የሶዶ ወረዳ ባህል ቱሪዝምጽ/ቤት የወረዳው ህዝቦች የባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ቅርስና ሥነ-ጥበብ እሴቶችን በማጥናት፣በማልማት እና በመጠበቅ የህብረተሰቡ ማንነት እንዲታወቅ ጽ/ቤቱ በአሁኑ ዘመን በዓለማችን በፍጥነት እያደገ የመጣውን የቱሪዝም  ዘርፍ በማጎልበት የወረዳው ተፈጥሮአዊ መስህቦችን በማልማትና ለዓለም በማስተዋወቅ በወረዳው ገጽታ ግንባታ ላይ ተገቢውን ድርሻ እያበረከተ ከመሆኑም ባሻገር በቱሪዝም ዘርፍ የወረዳው ገቢ በማሳደግ የማይናቅ ሚና በመጫወት በድህነት ቅነሳ ረገድ አስተዋጽዎ እያደረገ ይገኛል ፡፡ የወረዳችን ውብ የመሬት አቀማመጥና ማራኪ የተፈጥሮ ሀብት ያለው ሲሆን  ወረዳው የተለያዩ የዱር እንስሳትና ዕጽዋት ሀብት ባለቤት ነው፡፡ በተጨማሪም ለቱሪስት መስህብነት የሚሆኑ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ (መስቀል፤ገዳማት፤፣ዋሻዎችና ጥብቅ የተፈጥሮ ደኖች…) ሀብቶች ባለቤት ነው፡፡

Contact

Email-sodoweredacultureandturisemoffice@gmail.com

Telegram-t.me/sodoweredacultureandturisemoffice