ሶዶ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት

Sodo woreda Women and Children Affairs Office

ወ/ሮ ልኬለሽ ከበደ የሶዶ ወረዳ ሴ/ወ/ህ/ጉ/ጽ/ቤት ኃላፊ

ራዕይ

“በ2022 ሴቶች በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና በባህል መስኮች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት፤ የህፃናት መብትና ደህንነት የተከበረባት፤ የህፃናት መልካም ስብዕና የጎለበተባት እና የስርአተ-ጾታ እኩልነት የሰፈነባት ዞንን ማየት”፡፡

  • አሳታፊነትና ፍትሃዊነት፣
  • ግልጽነትና ተጠያቂነት፣
  • ፈጠራ፣
  • ቅልጥፍናና ውጤታማነት፣
  • የአገልግሎት ጥራት፣

የሴቶችን በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፤ የህፃናትን መብትና ደህንነት ማስጠበቅና የፆታ ዕኩልነትን ማስፈን፡፡

ለዚህምተፈፃሚነት፡-

  • የግንዛቤና ሁሉን አቀፍ ንቅናቄ መፍጠር፣
  • ሴቶችና ህፃናት እንዲደራጁ ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ማብቃት፣
  • በህጎች ፖሊሲዎችና የልማት ፕሮግራሞች የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መካተቱንና መፈፀሙን ማረጋገጥ፤ ማስተባበር፣ ክትትል ማድረግና ድጋፍ መስጠት፣
  • የሴቶች ልዩ ድጋፍ እርምጃዎች መፈፀማቸውንና ሴቶች በውሳኔ ሰጪነት ቦታ መመደባቸውን ማረጋገጥ
  • የህጻናት ስብዕና መገንባት
  • በቤተስብ ደረጃ ሴቶችን ውሳኔ ስጪነት ብቃት ማጎልበት
  • የሴቶች የልማት ፍንድ በማቋቋም ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ

የሴክተሩ ተልዕኮ

  • የወረዳው ሴ/ህ/ጉ/ጽ/ቤቱ 3 ዋና ስራ ሂደቶች ያሉት ሲሆን እነዚህም የሴቶች ንቅናቄ ተሳትፎ ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት፣ የሴቶች ህፃናት መብት ደህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬትና የሴቶች ህፃናት በልማት ማካተትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ናቸው ከእዚህም የሚሰሩት ስራዎች ሴቶች በልማት ቡድን፣ በማህበር፣ በመንደር ቁጠባ ብድርና፣ በጥቃቅን አነስተኛ፣ በዶሮ እርባታና በተለያዩ ዘርፎች በመሰማራቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ አቅማቸው በማጎልበት ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ችለዋል፡፡
  • ሴቶች ከባሎቻቸውና ለእማወራ ሴቶች ለብቻቸው የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንዲሰጣቸው ከሚመለከተው ተቋም ጋር እየሰራን መሆኑ
  • የሴቶችን ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎች እንዲጠቀሙ ከሚመለከተው ሴክተር መ/ቤት ጋር እየሰራን መሆኑ
  • እንዲሁም መስኖ ገብ የሆኑ መሬት ላላቸው የሴት ማህበራት የምርጥ ዘር ማዳበሪያና የጀነሬተር ድጋፍ በማድረግ የበጋ መስኖ ስንዴ ላይ እንዲሰማሩ ማድረግ ተችሏል፡፡
  • ሴቶች የተለያዩ ጥቃቶች ለአካላዊና ስነ ልቦናዊ ጥቃቶች ሲፈፀምባቸው የስነ ልቦና ምክር አገልግሎት፣ የማደራደር፣ የልጅ ቀለብ፣ የንብረት ክፍፍል እንዲሁም አቅም ለሌላቸው ሴቶች የነፃ ጥብቅና እንዲያገኙ የሚሰራ መሆኑ
  • ከህፃናት አንፃር የህፃናት መብት ከማስጠበቅ ከጉልበት ብዝበዛ፣ ጠፍተው የተገኙ ልጆች ከማቀላቀል፣ ጥቃቶች እንዳይፈፀምባቸው ለማህበረሰቡ በተለያዩ አማራጮች ግንዛቤ በመስጠት ህፃናቱን በህፃናት ፓርላማና ክበባት በማቋቋም ስልጠናዎች እንዲያገኙ በማድረግና በህዝብ ም/ቤቶች እንዲሳተፉ በማድረግ የሚሰራ መሆኑ
  • በአጠቃላይ የሴቶችና ህፃናት መብት ደህንነት ማስጠበቅም ሆነ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ሊያግዙ ይገባል ምክንያቱም ሴት ትውልድን ታስቀጥላለች ትውልድ ደግሞ ሀገርን ያስቀጥላልና ስለዚህ በሴቶችና ህፃናት ላይ በደንብ ተጋግዘን ልንሰራ ይገባል፡፡

Contact

Email-womensandchildrenaffairs@gmail.com

telegram-t.me/womensandchildrenaffair