ሶዶ ወረዳ ፍርድ ቤት
Sodo woreda Court
ዓላማ ፡-
የተቋቋመበት ዓላማ በክልሉ ሕገ መንግስት በተሰጠው ሕግን የመተርጎም ስልጣን በመጠቀም የዜጎችን ሰብዓዊ፣ዴሞክራሲያዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች በማክበርና በማስከበር ለወረዳው ሕዝብ፤ እንዲሁም ለሀገሪቱ ህዝብ ፍትሕን በእኩልነት በማስፈን እና ከማህበረሰቡ የሚቀርቡለትን በፍርድ ማለቅ የሚችሉ ጉዳዬችን በአገሪቱ ሀግ መሰረት ነጻ፣ገለልተኛ፣እና ተደራሽ በመሆን ክርክሮችን በተፋጠነ ሁኔታ ማየት እና ውሳኔ መስጠት ነው፡፡
ተልዕኮ (mission)
ከማናቸውም ተፅዕኖ ነፃ በመሆን ሕግን በመተርጎም ክርክሮች ላይ እልባት በመስጠት በሕግ የሚመራ የዳኝነት አካል በመፍጠር በገለልተኝነት፣በህዝብ አገልጋይነት ስሜት፣በቅልጥፍና፣በሚዛናዊነት ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡
በ2023 ዓ.ም ፍ/ቤታችን ገለልተኛና ነፃ በመሆን ፍትህን ለሁሉም በተፈለገው ጊዜ እና ጥራት በመስጠት መልካም ስምናዝና ያተረፈ ሆኖ ማየት
የፕሬዝዳንት መለክት
የዳኝነት አገልግሎትን ለማሻሻል መንግስት በርካታ የማሻሻያ ሥራዎች እየሰራ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ፍርድ ቤቶችም በየደረጃው የተሰጣቸውን ተልዕኮ መሰረት በማድረግ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት የዜጎችና የህብረተሰቡን ጥቅም ለማስከበር ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ህብረተሰቡ የሚያገኘው አገልግሎት በተመለከተ አሁንም የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሠጣጥ ችግሮች እንዳሉ በተለያየ ወቅት እንደሚያነሳ መረዳት ተችሏል፡፡ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት አገልግሎት ከአድሎ ያልፀዳና በተለያየ መልኩ የሚገለፅ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር የሚስተዋልበት መሆኑ በተለያዩ ህዝባዊ መድረኮች በሚነሱ የህዝብ አስተያየቶችእንዲሁም በቃልና በጽሁፍ ከሚቀርቡ ቅሬታዎች ያመለክታሉ፡፡በተለይ ፍርድ ቤቶች ላይ የሚነሱ የስነ-ምግባር ጥሰቶች ወንጅል ትግስት የማይደረግባቸው በመሆናቸው እዘህ ጥሰቶች ሲፈጸሙ ማህበረሰቡ ማገል እንዲችል ጥቆማዎች መቀበያ ዘዴዎችን ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከ ወረዳ ፍርድ ቤት አመራሮች ስልክ፣ ኢሜል፣ ማህብራዊ ድህረ ገጾች( ፌስ ቡክ፣ቴሌግራም ) መሰል አሰራሮች የተዘረጉ በመሆኑ ማህበረሰቡ ፣ በመጠየፍ የራሱን አስተዋጾ እንዲያደርግ እና ወደ ፍርድ ቤት ሲመጣ ከባለሙያ ጋር በመመካከር አስፋለጊ ማስረጃዎቹን አሟልቶ ሀቅን ብቻ ተማምኖ እንዲቀርብ እንዲሁም በገንዘቡ እና በዘመድ አዝማድ ጉዳዩን ለመጨረስ ከመሞከር እንዲቆጠብ አደራ እላለው፡፡
Contact
Email- Sodoweredafirdbet@gmail.com
Telegram :- t.me/sodowerdafirdbet