የሶዶ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት

Sodo woreda Justice Office

Email- sodoweredafiteh@gmail.com

የጽ/ቤቱ ራዕይ

በወረዳው ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተጠብቀው የህግ የበላይነት ተረጋግጦ በአገራችን በአርአያነት ሊጠቀስ የሚችል ፍትህ ሰፍኖ ማየት፡፡

የዕቅዱዓላማ

የዚህ ዕቅድ ዓላማ የወረዳው የፍትህ ጽ/ቤት የተጣለበትን ኃላፊነትና ተግባር በስትራቴጂያዊ አስተሳሰብበና ስልት መመራት የስትራቴጂያዊ መሠረቶችና ጉዳዮችን ትስስር በሚያጠናክ መልኩ ከባለ ድርሻ አካላት  በቅንጅት በመስራት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርነው፡፡

  • የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ
  • ታማኝነት፣ ግልፀኝነትና፣ ተጠያቂነት
  • ቀልጣፋነት፣ ፍትሐዊነት፣ ተደራሽነት እና ወጪ ቆጣቢነት፣
  • እኩልነትና የአልጋይነት ስሜት
  • ውጤትና አገልጋይነት ተኮር መሆን
  • የተቀናጀ የፍትህ አገልግሎት
  • ለለውጥ ዝግጁነት

ማስፈፀሚያ ስልቶች

  • የጽ/ቤቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በሚያሳካ መልኩ ምርጥ ተሞክሮዎችንና የላቁ ውጤቶችን በመቀመርና በማስፋት፣
  • የተደራጀ የለውጥ ሰራዊት በብዛትና በጥራት በማበራከት የለውጥ ተግዳሮት የመቀነስ ስልት በመቀየስ፣
  • የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የሚያዳክም ስልት በመቀየስ ቀልጣፋ፣ ፈጣን፣ ውጤታማና ተደራሽ ፍትሕ ለማስፈን የግልጸኝነትንና ተጠያቂነት አሰራርን በመፍጠር፣
  • የህብረተሰቡና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በማስፋትባለቤትነትና ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጥ ስልት በመንደፍ፣
  • የፈጻሚዎችን ውጤታማነት ሊያሳድግ በሚችል መልኩ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት፣
  • ወጥነትና ተከታታይነት ያለው የክትትልና ግምገማ ስርዓት በመዘርጋትና የመረጃ ፍሰትና ግብረ-መልስ አሰጣጥ ስርዓትን የተቀላጠፈ በማድረግ በየደረጃው ጥራት ያለው ውሳኔ እንዲኖር በማድረግ፣
  • ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን እንዲሻሻል ማድረግ፣
  • የጽ/ቤቱ ተልዕኮ በወረዳው ፍትህ እንዲሰፍን፣የመንግስትና የህዝብ ጥቅሞች እንዲጠበቁ፣በህገመንግስቱ ላይ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማስቻል የህብረተሰቡን ንቃተ ህግ በማሳደግ፣ወንጀል ፈፃሚዎች ለህግ እንዲ ቀርቡና ለፈፀሙት ጥፋት በሕግ እንዲጠየቁ በማድረግ እንዲሁም የህብረተሰቡንና የተቋማትን የመደራጀት መብት በማረጋገጥ የመሪነት ሚና በመጫወት የህግ የበላይነትንና መልካም አስተዳደርን ማስፈን

Contact

Email-sodoweredafiteh@gmail.com

Telegram:-t.me/sodoweredafiteh