Contac: Sodoweredasitoffice@gmail.com
ሶዶ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት
Sodo Woreda Youth and Sports Office
ራዕይ፡- በ2022 የወረዳው ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ስፖርትን በሀሉ ያደረገ ጠየናማ ማህበረሰብ መልካም ስብዕና ያለው ወጣት ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆኑ ስፖርተኞች ተፈጥረው ማየት ፡፡
ተልዕኮ፡- የወረዳን ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳፍፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና ህዝባዊ መሰረት ያለውን ስፖርት በማስፋፋት የዜጎችን አካላዊና ኢኮኖሚያዊ ብቃት በመገንባት ያገርን ብልጽግና ማረጋገጥ ፡፡
- አሳታፊና ፍታሀዊነት፤
- ግልጸኝነትና ተጠያቂነት፤
- ፈጠራን ማበረታታት
- ቅልጥፍናና ውጤታማነት፤
- የአግልግሎት ጥራት፤
- ለለውጥ ዝግጁነት፤
- በቡድን መስራት፤
- ህዝባዊነት፤
- በአካል እንቅስቃሴው የጎለበተ ብቁ ዜጋ መሆን እንዲችል በተከፈቱ የወጣት ማዕከላት በመገለገል ስፖርትን የባህሉ አንድ አካል እንዲያደርግ መደገፍ፤
- ራሱን ከልዩ ልዩ አደንዛዥ ዕጽ/ደባል ሱስ ጠበቆና ተከላክሎ አስተሳሰቡ ያደገ ቡቁና አምራች ዜጋ እንዲሆን ለለውጥ መስራት ፤
- በኢኮኖሚው ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ በማድረግና የስራ ባህሉን በማሳደግ ዘለቄታ ያለው ተጠቃሚነት እንዲኖረው ማድረግ
ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ስልጣንና ተግባር
- የወጣቶች መብትና ጥቅም በማስከበር ዙሪያ ግንዛቤና ንቅናቄ መፍጠር
- ወጣቶችን ሁኔታ የሚያመላክቱ ዝርዝር መረጃዎችን ያሰባስባል ፤ያደራጃል ፤ ለሚመለከተው ያሳውቃል
- ወጣቶች በወረዳው የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድሎች የተመቻቸላቸው መሆኑን ያረጋግጣል
- ወጣቶች በልማት መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ስራዓት ግንባታ ላይ ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ
- በወረዳው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራትን ያስተባብራል፤
- ወጣቶች በስነ ምግባር የታነጹና አውንታዊ አመለካከት እንዲያጎለብቱ የስብዕና ግንባታ ስራዎች ይሰራል ፤
- ወጣቶች ማዕከላትን በማስፋፋት ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙ ችሎታቸውና ዝንባሌያቸውን እንዲያጡ ድጋፍ ያደርጋል ፤
- የስፖርት ውድድሮች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፤ ያስተባብራል ፤
- የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል/ያስተባብራል ፤ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል
- የስፖርት ት/ት ስልጠና እንዲስፋፉ ያደርጋል ፤
- በግል ለሚቋቋሙ የስፖርት ስልጠና ምዕከላት ፍቃድ ይሰጣል ፤ ይመዘግባል ፤ ይሰርዛል ፤
05 ማጠቃለያ ፡- የሶዶ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከዚህ በላይ የተገለጸውን እንደ መነሻና ጥቅል ሀሳብ በማቅረብ ጽ/ቤቱ በአመታዊ ዕቅዶች በመያዝ ተግባራቸውን በዝርዝርና ስፋት ባለው ሁኔታ በቀጣይ የሚያቀርብ ሲሆን ለመጀመሪያ ደረጃ ስለጽ/ቤቱ ከራዕይና ተልእኮ ጋር በተያያዘ አሁን ያለበትን አቋም በተመለከተ በአጭሩ ባለው ሁኔታ ተገለጸውን ይመስላል፡፡
Contact
Email-sodoweredayouthsportoffice@gmail.com
Telegram-t.me/sodoweredayouthsportoffice
