ሶዶ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት.
Sodo woreda Labor and Social Affairs Office.
ተልዕኮ ( mission ) :-
- የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በሚመለከት የወጡ ፖሊሲዎችን ፤ አዋጆችን ፤ ደንቦችና መመሪያዎችንና ኮንቬንሽኖችን ተግባራዊ ማድረግ
- የህ/ሰቡ በተለይም የጎዳና ተዳዳሪዎች ፤ የአካል ጉዳተኞች ፤ አረጋዊያን ፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የህ/ሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ያደረገ ድጋፍ ማድረግ ፡፡ የማህበራዊ ችግሮችን መከላከልና ማህበራዊ ደህንነት ልማና የተሃድሶ አገልግሎቶችንማስፋፋትሠ
- የሴክተሩ የማስፈጸም አቅም በመገንባት በወረዳችን ጤናማ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት እንዲዳብር የሰራተኞች ደህንነትና ጤንነት እንዲጠበቅ የስራ አካባቢ እንዲጎለብት እና የስራ ስምሪት እንዲስፋፋ ማድረግ
2 . ራዕይ ( vision ) :-
በ 2020 የኢንዱስትሪ ሰላም የሰፈነበት የስራ ዕድሎች ተስፋፍተው ምርትና ምርታማነት ያደገበትና የማህበራዊ ችግሮች ተወግደው የህ/ሰቡ ማህበራዊ ደህንነት የጎለበተበት ወረዳ እውን ሆኖ ማየት ፤
- ታማኝነት
- ግልጽነትና ተጠያቂነት
- ፍትሃዊነትና እኩልነት
- አሳታፊነት
- ተባብሮ መስራት
- ቀጣይነት ያለው መሻሻል
- በእውቀት መምራት /መስራት/
- ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት
ውጤታማነት
- የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ደንበኞችን መሠረት ያደረገ ግንዛቤ በመፍጥር በዝቅተኛ ወጪ ቀልጣፋና ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው አገልግሎት በድህነት ፤ በመገለልና በተጋላጭነት አደጋ ውስጥ የሚገኙ የህ/ሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ፡፡
- ቀልጣፋና ዘመናዊ የሆነ የስራ ስምሪት አገልግሎት በመስጠት ስራና ሰራተኛን ለማገናኘትና በወረዳው የሚታዩ የስራ አጥነት ችግሮችን ለማቃለል ጥረት ማድረግ
- በስራ ምክንያት በሰራተኞችደህንነትና ጤንነት ላይ እንደዚሁም በልማት ድርጅቶች ሀብትና ንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችንና ጉዳቶችን መቀነስና የስራ ሁኔታዎችነንና የስራ አካባቢዎችን ማሻሻል ፡፡
- ሠራተኞችና አሰሪዎች በነፃ በመደራጀትና አደረጃጀታቸውን በማጠናከር መብትና ጥቅማቸውን እንዲያስጠብቁና የልማት ተሳትፎአቸውን እንዲያጎለብቱ ማብቃት
- በአሰሪዎችና በሰራተኞች መካከል ጤናማ የስራ ግንኙነት እንዲመሰረትና እንዲጠናከር ለማብቃት በመካከላቸው የሚፈጠሩ የስራ ክርክሮችን በስራ ቦታ በሁለትዮሽና በሶስትሽ እንዲሁም በስራ ክርክር ፈቺ አካላት ወቅታዊና ፍትሃዊ እልባት እንዲያገኙ ለማድረግ ፡፡
- አሰሪዎች ሰራተኛና ባለድርሻ አካላት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ፤ ህጎችና ሌሎች የህግ ማዕቀፎች ላይ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ፡፡
የተቋሙ የትኩረት መስኮች
- የስራ ገበያ መረጃ ስረዓትን ማጠናከርናማሳደግ ማህበራዊ ደህንነትን ማረጋገጥ
- የማህበራዊ ጥበቃስርዓትን መዘርጋትየስው ሃይል ማልማት
- የስራ ስምሪት አገልግሎት ማስፋፋት
- ህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል
Contact
Email-sodoweredaserategnanamahberawi@gmail.com
Telegram-t.me/sodoweredaserategnanamahberawi