ሶዶ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት

Sodo Woreda Peace and Security Office

አቶ ዳዊተ ጉግሳ የሶዶ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ

ተልዕኮ

የወረዳውን አስራርና አደረጃጀት ዘመናው በማድረግ ግጭትን፣ የሀይማኖት አክራሪነት  በበቃት ለመከላከል የሚያስችል የፀጥታ መረጃ ስርዓት በመፍጠር በህ/ሰቡ ንቁ ተሳትፎ የሚታገዝ የፀጥታ አስከባሪ ሀይል እንዲኖር በማድረግ የህግ ታራሚዎችንና የዜጎችን ሰብሀዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በማስጠበቅ ሰላምና ፀጥታን ማስከበር፡፡

                1.2 ራዕይ

የዜጎች ሰብሀዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶች ማስከበር፣ሰላምና ፀጥታ ማስፈን፣ የህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር የተረጋገጠበት ወረዳ እንዲሆን የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፆ የሚያበረክት ተቋም ሆኖ ማየት፡፡

  • የሕብረተሰቡን ፀጥታና ደህንነት ማስጠበቅ ተግባራችን ነው
  • ለህግ የበላይነት ቆመናል
  • ፍትሀዊነት ታማኝነት መለያችን ነው
  • የህዝብ አገልጋይነት መርሀችን ነው
  • ግልፅነትና ተጠያቂነት መታወቂያችን ነው
  • አሳታፊነት መርሀችን ነው
  • ሚስጥር መጠበቅ ቃል ኪዳናችን ነው፡፡
  •  

የሶዶ ወረዳ የሰላምና የፀጥታ ሀላፊ አስተያየት

ከመላው ማህበረሰቡ ጋር እና ከሌሎች አጎራባች  ወረዳዎች ጋር ሰላማዊ የሆነ ግንኙነት ያለው እና የወረዳውንም ህዝብ ከወረዳው መንግስት ጋር በመሆን የወረዳው ሰላም ለማስጠበቅ የሚተጋ ሲሆን ጥቃቅን ችግሮችን እንኳን ቢኖሩ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በውይይት የውስጥ ችግሩን የሚፈታ ማህበረሰብ ያለበት ወረዳ መሆኑን የበለጠ የልማት፤የፖለቲካና ማህበራዊ ግንኙነቱ የበለጠ ከፍ እንዲል ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሲሆን በተጨማሪ አገር ፈተና ውስጥ በገባበት ወቅት ከወረዳው የተወጣጡ ወጣቶች የአገር ዳር ድንበር ለማስጠበቅ እስከ ግንባር ጭምር በመዝመት የህዝብና የአገር አደራ እንዲወጣ ትልቅ አስተዋፅዎ ያደረገ ሲሆን

አውንም የወረዳው ህዝብ የሚመለከተው ባለድርሻ አካላት አካባቢውን ከፀረ ሰላም ኃሎች እየጠበቀ የተለመደውን የልማታ፤ፖለቲካ ፤የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ግንኙነታችንና ስራዎቻችን በጠበቀ መንገድ ማገዝ እንዳለብን መልክቴን አስተላልፋለሁኝ፡፡

Contact

Email-sodoweredaselamnatseteta@gmail.com

Telegram-t.me/sodoweredaselamnatseteta